መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 2፤2014-ፕሬዝዳንት ማክሮን የዩክሬን ቀውስ እንደማይባባስ ፑቲን አረጋግጠውልኛል ሲሉ ተናገሩ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩስያ ሀይሎች በዩክሬን ድንበር አካባቢ ያለውን ቀውስ እንዳይጨምር አደርጋለሁ በማለት ቃል ገብተዉልኛል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ፑቲን ከዩክሬን መሪዎች ጋር ተገናኝተዉ ከመምከራቸዉ በፊት ምንም ነገር መበላሸት ወይም መባባስ እንደማይኖርበት ማረጋገጫ ሰጥተዉኛል ሲሉ ማክሮን ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር እቅድ አላት መባሉን ብታስተባብልም፣ ከ100,000 በላይ ወታደሮቿን በድንበር አካባቢ አስፍራለች፡፡በሞስኮ፣ በዩክሬን እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ያለው ውጥረት ያገረሸዉ ሩሲያ የዩክሬንን ደቡባዊ ግዛት የነበረችዉን የክራይሚያ ልሳነ ምድር ወደ ራሷ ከቀላቀለች ከስምንት ዓመታት ገደማ በኋላ ነው።

ለቀዉሱ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲኖር ጥረት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ማክሮን ሰኞ እለት በሞስኮ ከፑቲን ጋር ለስድስት ሰአታት የሚጠጋ ዉይይት ካደረጉ በኋላ ትላንትና ወደ ዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ገብተዋል።ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማክሮን እንደተናገሩት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚደረገዉ ድርድር ወደፊት ለማራመድ እድል እንዳለ እና ውጥረቶችን ለመቀነስ ተጨባጭ መፍትሄ ማየት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *