መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 7፤2014-በኢትዮጲያ የሰገራ ንቅለ ተከላ ህክምና እንደሚሰጥ ያውቃሉ

❖ የሰገራ ንቅለ ተከላ በአብዛኛው ለአንጀት ኢንፌክሽን የሚሰጥ ህክምና ሲሆን በተጨማሪም ተደጋጋሚ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ አንቲባዮቲክ የሚወስዱ ሰዎች ለዚህ ህመም ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡

ህክምናው የሚሰጠው ሰገራ ውስጥ የሚገኝ ጠቃሚ ባክቴሪያ ከለጋሹ ህክምና ለሚያስፈልገው በማስተላለፍ ነው፡፡

የሚለግሱ ሰዎች ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄ ምንድን ነው?

❖ የሚለግሱት ሰገራ እንደሌላ የንቅለ ተከላ ዓይነቶች መመሳሰል አለበት የሚል ነገር አይኖርም ሆኖም የቤተሰብ ከሆነ 93 በመቶ ህክምናው ስኬታማ ይሆናል።ከቤተዘመድ ውጪ 83 በመቶ ነው፡፡

❖ ለጋሹ ምንም ዓይነት አደንዛዥ እፅ የማይጠቀም እና ንቅሳት የሌለበት መሆን ይገባዋል።

❖የሰገራ ለጋሹ ከመለገሱ አስቀድሞ ለሁለት ወራት አንቲባዮቲክ መድኃኒቶችን ያልወሰደ መሆን አለበት፡፡

❖የደም ናሙና በመስጠት ኤች አይቪ የጉበት በሽታን ጨምሮ የአበላዘር በሽታ ነፃ መሆን አለበት።

❖ ለጋሹ አስቀድሞ ሰገራውን በመስጠት አላስፈላጊ ተዋስያን መለየት እንዳለባቸው ዶ/ር ናኦል አብዲ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የተቀባዩ ቅድመ ጥንቃቄ ምንድን ነው?

❖ ንቅለ ተከላው ከመደረጉ አንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ ምንም ዓይነት መድኃኒት መውሰድ የለበትም።

የሚሰጥበት መንገድ እንዴት ነው?

❖ ህክምናው ከሰገራ ውስጥ ጠቃሚ ባክቴሪያ ያለውን በፈሳሽ መልክ በትቦ ተደርጎ በአፍንጫ እና በአፍ በኩል አንጀት ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል።

❖ አሁን አሁን በኪኒን መልክ መሰጠት ተጀምራል፡፡

❖የሚለገሰው ሰገራ በሚለገስበት ወቅት የቆየ መሆን የለበትም።

በኢትዮጵያ ይሰጣል?

❖ በኢትዮጵያ በስፔሻላይዝድ እና በቴርሸሪ ሆስፒታሎች በዘርፉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ይሰጣል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *