መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 7፤2014-ኢትዮጵያ ለፍቅረኞች ቀን አበባን ወደ ውጪ በመላክ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

የፍቅረኛሞችን ቀን ምክንያት በማድረግ 2,700 ቶን የአበባ ምርት ወደ ውጪ ሀገራት በመላክ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የአበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር አስታወቀ፡፡የማህበሩ የማስታወቂያና የመረጃ አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ የምሥራች ብርሃኑ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የአበባ ምርቱ የተላከው ባለፉት 13 ቀናት ውስጥ ሲሆን ዋነኛ መዳረሻው ኔዘርላንድ ቢሆንም በተጨማሪም ወደ ተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት እና ወደ መካካለኛው ምስራቅ ሀገራት መላክ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ የአበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር በስሩ ከአበባ በተጨማሪ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን የሚያቀርቡ በአጠቃላይ 120 አምራች ላኪዎች ይገኛሉ፡፡ከነዚህ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑት የአበባ አምራችና ላኪዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ከአበባ ዘርፉ ባላፈው 2013 አመት 531 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷ ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የአበባ ልማት በአፍሪካ ከጎረቤት ኬንያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 4ኛ ይገኛል፡፡የአበባ ልማት በ1,600 ሄክታር መሬት ላይ በኦሮሚያ፣በአማራ እና በደቡብ ክልሎች በአገር ውስጥና በውጭ አልሚዎች እየተከናወነ ይገኛል ሲሉ ወ/ሮ የምሥራች ብርሃኑ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *