መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 7፤2014-ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከአህያ ስጋ የወጪ ንግድ 190 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ አገኘች

ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 168 ቶን የአህያ ስጋ እና ቆዳን ወደ ቻይና የላከች ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት 190 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፤ይህ አፈጻጸምም ከታቀደው አንጻር የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑንም በኢንስቲትዩቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበሌ ለማ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ፡፡

ከሌሎች የአለም ሃገራት በበለጠ ቻይና ከፍተኛ የሆነ የአህያ ስጋና ቆዳ ፍላጎት እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ኢትዮጲያ ባለፉት ስድስት ወራት በአንድ ዙር የአህያ ስጋን ወደ ቻይና ልካለች፡፡አቶ ደበሌ አክለውም እስካሁንም ድረስ አርሶ አደሩ ለተለያዩ አገልግሎቶች የማያውላቸውን የአህያ እንስሳት በመምረጥና በባለሙያ ጥናት በማድረግ ለዚሁ አላማ እንዲውሉ ሲደረጉ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል ፡፡

ኢትዮጵያም ከአህያ ስጋ ምርት የወጪ ንግድ በቀጣይ የተሻለ ገቢን እንድታገኝ ለማድረግ በዚሁ ስራ የተሰማራው የአሰላ ቄራ ድርጅት ያለውን የእርድ አገልግሎት አቅሙን እንዲያጠናክር እና ሎሎች ኢንቨስተሮችንም በዘርፉ እንዲሰማሩ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰሩም ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡

በቅድስት ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *