በሸዋሮቢት ከተማ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀዉ የህወኃት ቡድን በቆየባቸው አስራ ሁለት ቀናት በከተማዉ ሰብዓዊ ጥፋት እና የኢኮኖሚያ ዉድመት ማድረሱ ይታወሳል፡፡ ሸዋሮቢትን መልሶ የመገንባት ስራዎች እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በጤና ተቋማት ላይ ቡድኑ ጉዳት እንዳያደርስ የህክምና መሳሪያዎችን ቀድሞ ለማውጣት ተችሎ የነበረ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ስራ መግባት መቻሉን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አጥላው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ሸዋሮቢትን በተቻለ መልኩ ወደነበረችበት የመመለስ ስራ እየተሰራ ያለ ቢሆንም አሁንም ድረስ በትምህርት ቤቶች ላይ በከፊልም ቢሆን ያልተሞሉ የመማሪያ መሳሪያዎች ስለመኖራቸው ተገልጾል፡፡
አያይዘውም በኑሮ ውድነት ዙሪያ የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ ለማረጋጋት እየተሰራ ያለ መሆኑን የገለጹ ሲሆን የበርበሬ እንዲሁም ለመሰረተ ልማት የሚያገለግሉ የግንባታ መሳሪያዎች ግን አሁንም በእጥፍ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አጥላው በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በኤደን ሽመልስ