መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 8፤2014-የኢትዮጵያዊቷ ሥራ ፈጣሪ አጊቱ ጉደታ ገዳይ የ20 ዓመት እስራት ተፈረደበት!

በጣሊያን የትሬንቶ ፍርድ ቤት ትናንት የካቲት 07 ቀን 2014 በዋለው ችሎት በኢትዮጵያዊቷ ሥራ ፈጣሪ አጊቱ ጉደታ ላይ አሰቃቂ ጥቃት በማድረስ ለህልፈተ ህይወት የዳረገው የ33 ዓመቱ ጋናዊ ሱሌማን አዳምስ ላይ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶበታል።

አጊቱ በትሬንትኖ ሊጠፉ የተቃረቡ የፍየል ዝርያዎችን ከመጥፋት በመታደግና ፍየል እርባታ፣ በአካባቢ እንክብካቤ፣ በወተትና ወተት ተዋፅኦ ምርት በጣም ውጤታማ የነበረች እና በጣሊያን ህዝብና መንግሰት እንዲሁም በዳያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ በውጤታማነቷ ሞዴል የነበረች ትጉህ ሴት ነበረች ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

ለዚህ ፍትህ መገኘት የአካባቢው የመንግስት ኃላፊዎችና ነዋሪዎች እንዲሁም የትሬንቲኖ የኢትዮጵያ ዳያስፓራ ኮሚኒቲ በጣሊያን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጋር በመስራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ኤምባሲው ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *