መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 9፤2014-በሶማሊያ ዋና ከተማ ከባድ ፍንዳታ እና የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ ተሰማ

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ትላንት ረፋድ ላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች በፖሊስ ጣቢያዎች እና በፍተሻ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን የመንግስት ባለስልጣናት አስታውቀዋል።በሃገር ውስጥ የሰዓት አቆጣጠር መሰረት 1፡00 አካባቢ ከባድ የተኩስ ድምጽ እና በርካታ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

ሆኖም የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሩ አብዱላሂ ኖር በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ከሆነ የፀጥታ ሀይሉ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ታጣቂዎች ድል አድርጓል ሲሉ ጽፈዋል።በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰ ጉዳት እና ሞት ግን እስካሁን ድረስ የተነገር መረጃ የለም።

ባለፈው ሳምንት በሀገሪቱ እየተካሄደ ባለው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ምርጫ ላይ የተሳተፉ ልዑካን ላይ ባነጣጠረ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸዉ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *