
በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውን ህወኃት ከአሸባሪ ዝርዝር ውስጥ ይውጣ ለሚሉ ጥያቄዎች መንግስት ምንም አይነት ምላሽ የለውም ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።አምባሳደር ዲና በዛሬው እለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ማብራሪያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ የደህንነት ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አካላት ተደራደሩ እያሉ ነው፤ ለምን አላችሁ የምንለው ነገረ የለም መንግስት ግን የራሱን አቋም ያራምዳል ለጥያቄው ምንም ምላሽ የለውም ሲሉ አስረድተዋል።ከተለያዩ አካላት ህወሃትን ከአሸባሪ ዝርዝር ውስር ይወጣ እያሉ ጥያቄ ቢያቀርቡሙ በመንግስት በኩል ምንም ምላሸ የለም ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ስለ አፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም ስለመጠናቀቅ ያነሱ ሲሆን በጉባኤው የ23 ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ፣ ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሮችና ሶስት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መገኘታቸውን ገልጣልቃ ።ጉባኤው ካተኮረባቸው ጉዳዮች መካከል ኮቪድ እና መፍትሄው ፥ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና የልማት አጀንዳ መሆናቸውን አስታውሰዋል።
በጉባኤው የሰላም እና ጸጥታ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የጠመንጃ ድምጽ በአፍሪካ አህጉር እንዳይሰማ የተያዘው እቅድ ሊሳካ አለመቻሉ አሳዛኝ ሲሉ አምባሳደር ዲና ገልፀውታል።እንዲሁም በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት መፈንቅለ መንግስት መብዛቱ አሳሳቢ መሆኑ የተነሳ ሲሆን እንዲሁም በአፍሪካ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ ስለሚኖር ጣልቃ ገብነት የጉባኤው ተሳታፊዎች ነቅፈውታል።
በቤቴልሄም እሸቱ