መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 10፤2014-ሩሲያ ወታደሮቿን ከዩክሬን ድንበር አካባቢ እያስወጣች ነዉ በሚል የተነገረዉ መረጃ የሀሰት ነዉ ስትል አሜሪካ አስታወቀች

ሩሲያ ወታደሮቿን ከዩክሬን ድንበር አካባቢ እያስወጣሁ ነው ማለቷ የሀሰት ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡ በቅርብ ቀናት ውስጥ 7,000 ተጨማሪ ወታደሮች ወደ ድንበራማዉ ስፍራ መስፈራቸዉን ስማቸዉ ያልተጠቀዉ ባለስልጣን ገልፀዋል።

ባለሥልጣኑ በተጨማሪም ሩሲያ ዩክሬንን “በማንኛውም ቅጽበት” ለመውረር “የሐሰት” ሰበብ ልትጠቀም እንደምትችል ተናግረዋል፡፡ሞስኮ በበኩሏ ወታደራዊ ልምምዷን እንዳጠናቀቀች እና ወታደሮቿም ከዩክሬን ድንበር እየለቀቁ መሆኑን አሳዉቃለች፡፡ነገር ግን ምዕራባውያን መንግስታት ከድንበራማዉ ስፍራ የሩሲያ ወታደሮቿ ለቀዉ ስለመዉጣታቸዉ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃ እንዳላዩ ተናግረዋል ።

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ በትላንትናዉ እለት በስልክ ባደረጉት ዉይይት የተባባሰዉን ዉጥረት ለማርገብ ሩሲያ ትክክለኛ እርምጃዎችን መውሰድ አለባት ሲሉ የጀርመኑ ቻንስለር ገልጸዋል። ሩሲያ ከ100,000 የሚበልጡ ወታደሮችን በድንበር አካባቢ ብታሰፍርም ዩክሬንን ለመውረር እቅድ እንደሌላት በተደጋጋሚ ታስተባብላለች፡፡

ነገር ግን የዋይት ሀውስ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉት በቅርብ ቀናት ውስጥ ትላንትናን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ አካባቢው አቅንተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *