መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 10፤2014-በሶማሊያ ጋዜጠኞችን ላይ ግፍ የፈጸሙ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዋለ

የሶማሊያ መንግስት በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በአልሸባብ የተፈጸመውን ጥቃት ለምን ትዘግባላችሁ በሚል ጋዜጠኞች ላይ በደል የፈጸሙ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታዉቋል፡፡የሶማሊያ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር አብዱላሂ ኑር “የታጠቁት ኃይሎች ለድርጊታቸው ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሶማሊያ መንግስታዊዉ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞቹ ዓይናቸውን፣ እጅና እግራቸዉን በማሰር መሬት ላይ ተኝተው የሚያሳይ ፎቶ በትዊተር ገፁ ላይ አጋርቷል፡፡የፖሊስ መኮንኖቹ በሶማሊያ የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ላይ በሚሰሩ ጋዜጠኞች ላይ ያነጣጠረ ድርጊት የፈጸሙ ሲሆን ባሳለፍነዉ ማክሰኞ በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ አልሻባብ የፈጸመዉን ጥቃት ለመዘገብ በሄዱበት የግፍ ተግባር ተፈጽሞባቸዋል፡፡

የአልሸባብ ታጣቂዎች ባሳለፍነዉ ማክሰኞ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ከፈጸሙ በኃላ በሞቃዲሾ የሚገኝ የፖሊስ ጣቢያን መዉረራቸዉ ይታወሳል፡፡በሶማሊያ ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች ከበርካታ አቅጣጫዎች ማስፈራራት፣ እስራት እና ጥቃት በተደጋጋሚ ይደርስባቸዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *