
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር በርካታ ቅርሶች በግለሰቦች እጅ ስር መገኘታቸዉ እና በግልነት የተመዘገቡ መሆናቸው ይዞታቸውን እንዲለቁ እያደረገ ይገኛል ይህም ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን የድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ ግለበሶች እጅ ላይ የሚገኙ ቅርሶችን ወደ ሙዚየም ለማስገባት ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገልፆል፡፡የድሬዳዋ የቱሪዝም መዳረሻ በርካታ ሲሆን በዋናነት ምድር ባቡር ተጠቃሽ ነዉ፡፡ይህንኑ መነሻ በማድረግ ከድሬዳዋ እስከ ደወሌ ለቱሪስቶች ክፍት አድርጓ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥቅም ላይ እንዲዉል ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ጥናት እና ምርምር እየተደረገበት ባለዉ የሀርላ ቅርስ ላይ በቦታው ሳንቲሞች፣ የተለያዩ ቅርሳ ቅርሶች እየተገኙ ይገኛል፡፡በህብረተሰብ ጥቆማ እና በቁፋሮ አሁንም የተለያዩ ቅርሶች እየተገኙ ሲሆን አካባቢው እንዲጠበቅ የማድረግ ስራ እንዲሁም በቀጣዮች 15 ቀናት ውስጥ በአካበባቢው ሙዚየም እንደሚከፈት ተገልፆል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት የድሬዳዋን ከተማ ከጎበኙ ከ47 ሺ በላይ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አቶ ሚካኤል እንዳለ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም