መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 10፤2014-ከሞያሌ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በተከሰተው የተሽከርካሪ አደጋ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ የዞኑ የኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ አብርሃም መኩሪያ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ የደረሰ ሲሆን መነሻውን ከሞያሌ አድርጎ በያቤሎ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዙ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 34983 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ደርሷል።ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ አቶ አብርሃም መኩሪያ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *