መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 10፤2014-የላይቤሪያ የቀድሞ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የላይቤሪያ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት የነበሩት አሞስ ሳውየር በ76 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ አሁን በእስር ላይ የሚገኙትና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቻርለስ ቴይለር የጀመሩትን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም በተደረገው ጥረት በሀገሪቱ ከፍተኛ እውቅና ካገኙ ፖለቲከኞች መካከል አሞስ ሳዉየር አንዱ ነበሩ።

ቻርለስ ቴይለር እና የኤን.ፒ.አፍ.ኤል አማፂያን ለሳዉየር አመራር እዉቅና በመንፈግ ከዋና ከተማዋ ሞንሮቪያ ውጭ በአራት አመታት ጊዜያዊ የአመራር ወቅት እንዳይዘዋወር ከልክለዉ ነበር፡፡ከጦርነቱ በኋላ ላይቤሪያ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ መምህር እና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር በመሆን ያገለገሉት ሳዉየር የመንግስት አስተዳደር ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል።

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *