መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 10፤2014-የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታግደዉ የነበሩ አገልግሎቶችን መስጠት ሊጀምር ነዉ

በታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀመሩ የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጅንሲዉ ከዚህ ቀደም በአገር አቀፍ ደረጃ ከአዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ውጪ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከሰኞ የካቲት 14 2014 ጀምሮ የሚጀመሩ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

በመሆኑም በሁሉም ክፍለ ከተማ በየወረዳው በተዘጋጀ መርሃ ግብር ነዋሪው መስተናገድ የሚችል መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሌብነትን በመፀየፍ ፤ ስጋት እየሆነ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ በመስራት የሚደረግ ማጭበርበርን ማህበረሰቡ እንዲከላከልም ኤጀንሲዉ ጥሪዉን አቅርቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *