መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 10፤2014-የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ የራሱን “ድሮን” በመሥራት የተሳካ የሙከራ በረራ አደረገ

የኬሚካል ምኅንድስና ምሩቅ የሆነው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር አማኑኤል ባልቻ ድሮን በመሥራት የተሳካ የሙከራ በረራ ማድረጉ ተገለጸ፡፡የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ፣ መምህሩ የሠራው ድሮን 250 ሜትር በተሳካ ሁኔታ በበረራ መሸፈን እንደቻለ አስረድተዋል፡፡

መምህር አማኑኤል ባልቻ፣ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሜካኒካል ምኅንድስና ተመርቆ በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን፤ ሁለት ድሮን እና አንድ አውሮፕላን እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ዩኒቨርሲቲው “የፈጠራ ቀን” በዓሉን በፓናል ውይይትና የተማሪዎቹን የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች በአውደ-ርዕይ በማሳየት እንዳከበረ ተገልጿል፡፡

በመርሃ-ግብሩም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እየሠሯቸው ላሉ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንዳለ እና በፈጠራ ሥራዎቻቸው አርዓያ የሆኑ ተማሪዎች ሽልማትና እውቅና እንደተበረከተላቸው ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እንደ ድሮን፣ የቡና መፈልፈያ ማሽን፣ የእንጨት መላጊያ፣ የጨርቃ ጨርቅ መሥሪያ ማሽኖች፣ የተለያዩ መሣሪያዎች መለዋወጫ፣ የዶሮ ማስፈልፈያ ማሽን(ኢንኩቤተር)፣ የተለያዩ አይነት ተሽከርካሪዎች፣ የውሃ መሳቢያ ሞተር፣ የሕጻናት ንፅህና መጠበቂያ ዳይፐር እና የመሳሰሉት ላይ በመርሃ-ግብሩ አካቶ እየሠራ እና እያበለጸገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *