መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 14፤2014-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው ልዩ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ይሾማል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ከዚህ በፊት ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የተገኘውን ግብዓት ምክር ቤቱ ከተመለከተ በኋላም መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን እጩ ኮሚሽነሮች በመምረጥ እንዲሾሙ ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

 1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
 2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ
 3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ
 4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ
 5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን
 6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ
 7. አቶ ዘገየ አስፋው
 8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም
 9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር
 10. አቶ ሙሉጌታ አጎ እና
 11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ እጩ ኮሚሽነር ሆነው ቀርበዋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው ልዩ ስብሰባ በእነዚህ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከተወያየ በኋላ ይሾማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *