መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 14፤2014-የጦር መሳሪያ እና ፈንጂ በህገወጥ መንገድ ይዘው የተገኙ ግለሶቦች በእስራት ተቀጡ

በሰሜን ሸዋ ዞን ወንጪ ወረዳ ዞን በአንድ ሆቴል ውስጥ የመኝታ ክፍል ተከራይቶ የነበረዉ ፊጣ ወይሳ የተባለዉ ግለሰብ ላይ በተደረገበት ድንገተኛ ፍተሻ 112 የተለያዩ የጦር መሳሪያ የተያዘበት መሆኑን ተከትሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ የኮሚኒኬሽን ክፍል ባለሙያ የሆኑት ሳጅን ልጅአሉ ከድር በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

ተከሳሹ መሳሪያዎቹን ሊያዘዋውር ሲል እጅ ከፍንጅ በመያዙ በምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በአምስት አመት ከስድስት ወር እንዲሁም ሶስት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ተላልፎበታል

በተመሳሳይ በሶዶ ዳኬ ወረዳ ወርቁ በቀለ የተባለ ግለሰብ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በሶዶ ዳኬ ወረዳ ከሪሸኖ በተባለ አካባቢ በመኖሪያ ቤት ውስጥ የተለያዩ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች እና ኤፍ ዋን ቦምብ አከማችቶ በመገኘቱ ፖሊስ ምርመራ ሲያደርግ ቆይቶ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በአምስት አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ተላልፎበታል፡፡

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *