መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 9፤2014-የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ሳቢያ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ገለፁ

👉 500 አባዎራዎች በአንድ ቆጣሪ ለመጠቀም ተገደዋል !!

ኮዬ ፈጬ 2 ተብሎ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ እድለኞች ከተላለፉ በኃላ ኑራቸውን በእዚያ ያደረጉ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል ሲሉ ለብስራት ሬዲዮ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

የቤት ባለ እድል መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ የነበረው የኤሌክትሪክ ችግር እስከ መስከረም ወር ይፈታላችኋል ብንባልም ችግሩ ሳይፈታ ህዳር ወርን ለማጋመስ ተገደናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች በተወካያቸው አማካይነት ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ከእዚህ ቀደም ችግሩን በጊዜያዊነት መቅረፍ ያስችለዋል የተባለለት የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በእያንዳንዱ ህንፃ ላይ ይገባላችኋል ብንባልም ይህ መሆን ባለመቻሉ ለፕሮጀክቱ መስሪያ ተብሎ በተዘጋጀ አንድ ቆጣሪ ላይ እስከ 500 የሚሆኑ አባወራዎች ለመጠቀም መገደዳቸውን ተወካዩ ገልፀዋል፡፡

ችግሩ ያልተቀረፈው አስቀድሞ መሰራት የነበረባቸው መሰረተ ልማቶች ባለመጠናቀቃቸው የተነሳ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ አስቀድሞ ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው የመሰረት ልማት ጥያቄዎች ካልተሟሉ የመብራቱን ችግር መቅረፍ በእጀጉ እንደሚያዳግት ተናግረዋል፡፡

በናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *