መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 12፤2014-በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል

በኦሮሚያ ክልል ከህዳር 5 እስከ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ13 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በ16 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ24 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በንብረት ላይ የደረሰዉ ዉድመት በገንዘብ ሲተመን ከ830 ሺ ብር በላይ እንደሚገመት በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መረጃ ጥናት እና አገልግሎት ዲቪዥን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋዎቹ በሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶና ደገም፣ በምስራቅ ጉጂ ዋደራ ፣በጅማ ዞን ዶማ ፣ በምዕራብ ሸዋ ሊበን ዳዊ ፣ ቦረና ዞን ያበሎ ፣በአዲስ አበባ ልዩ ዞን ሰበታ ወረዳዎች፣ ሻመመኔ እና ጅማ ከተማዎች የደረሱ ናቸው፡፡

አደጋዎቹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት የተመዘገቡ ሲሆን አብዛኛዎቹ የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት፣በህዝብ ማመላለሻ እና በሞተር ሳይክል ተሸርከርካሪዎች የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን ፣መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ የጥንቃቄ ጉድለት ፣ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር፣ መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *