መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 12፤2014-ቱርክ በኢስታንቡል ለደረሰው ጥቃት ሂሳብ ማወራረዷን አስታወቀች

ቱርክ በኢራቅ እና በሶሪያ በሚገኙ የኩርድ ታጣቂዎች ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች፡፡ በኢስታንቡል ከሳምንት በፊት የደረሰዉን የቦምብ ጥቃት ያቀነባበሩት የኩርድ ታጣቂዎች ናቸዉ ስትል ቱርክ ተጠያቂ ማድረግ ይታወሳል። ዘመቻዉ ጥፍር ሰይፍ የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ሲሆን በቱርክ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ይጠቀሙበታል የተባለዉን የኩርድ ጦር ሰፈርን መምታቱን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሶሪያ-ኩርዲሽ ቃል አቀባይ በበኩሉ እንዳስታወቀው ተፈናቅለዉ የነበሩ የሁለት መንደር ነዋሪዎችን የጎዳ ጥቃት ብሏል። የኩርድ ፒኬኬ ቡድን የኢስታንቡል ጥቃት ፈጽሟል መባሉን አስተባብሏል።የአየር ጥቃቱ እንደተጀመረ የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ተዋጊ አዉሮፕላን ሲነሳ የሚያሳይ እና የፍንዳታ ምስል በማከል “የሂሳቡ ሰአት” ደርሷል ሲል ትዊት አድርጓል።

የቱርክ መከላከያ ሚንስትር ሁሉሲ አካር “የአሸባሪዎች መጠለያዎች፣ ጉድጓዶች፣ ዋሻዎች እና መጋዘኖች በተሳካ ሁኔታ ወድመዋል” ሲሉ ተናግረዋል። የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር በሰሜን ሶሪያ እና በሰሜን ኢራቅ በሚገኙ የኩርድ ታጣቂዎች የጦር ሰፈር ላይ ባደረሰው ጥቃት 89 ይዞታዎች ወድመዋል፡፡በሶሪያ የሚገኙ የኩርድ ሃይሎች አፀፋውን ለመመለስ ቃል የገቡ ሲሆን የኮባኔ ከተማ እንዲሁም በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸው ሁለት መንደሮች መጎዳታቸውን በቁጭት ተናግረዋል ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *