መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 12፤2014-ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ውሃ መያዣ ቀለምን በማስቀረቷ በዓመት 50ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሏ ተነገረ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የውሃ ምርትን በተመለከተ ያሉበትን እንከኖች ለመፍታት የምርምር ጥናቶችን እያደረገ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ከምርምር ውጤቶች መካከል በዋናነት የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ቀለም በማስቀረት ዙሪያ በተደረገው ጥናት መሰረት ተግባራዊ በመደረጉ እንደ ሀገር ሊታጣ የነበረ 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የውሃ ፕላስቲክ ማሸጊን መልሶ የመጠቀም ተግባር በተመለከተ በተደረገው ጥናት ሙሉ በሙሉ መተግበር የሚስችል ሁኔታ ላይ በመደረሱ በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ወደ ስራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም እንደሚንስትሩ ገለጻ አምራች ኢዱስትሪዎችን በመደገፍ መንግስት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉ ሲሆን መሬት በማቅረብ ፣የፋይንስ፣ የኤሌክትሪክና ከግብአት ተያይዞ ያሉትን ችግሮች በማስቀረት በተለየ ደግሞ ከምርታማነት ጋር ተያይዞ የማምረት አቅም ካለመጠቀም ጋር ያሉትን ችግሮች በመፍታት የተደረጉ ሰፊ ጥረቶች መኖራቸውን ተናግረዋል ፡፡

አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ማምረት ብቸኛው አማራጭ ነው የሚሉት ሚኒስትሩ ከንግድ እና ከሌሎች የአገልግሎት ሴክተሮች ባሻገር ወደ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በመግባት ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር በገበያ ውስጥ ያሉትን እጥረቶች በመሸፈን አለፍ ሲል ደግሞ ኤክስፖርት ለማድረግ የሚቻልበትን እድሎች ማመቻቸት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።

በቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *