መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 12፤2014-ወራቤ ዩኒቨርስቲ ለደቡብ ኮሪያው ዮንግናም ዩኒቨርስቲ ስልጠና ሊሰጥ ነዉ

ወራቤ ዩኒቨርሲቲና ከደቡብ ኮሪያዉ ዮንግናም (Yeungnam) ዩኒቨርሲቲ ጋር በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ግብርና እና የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ስምምነቱ ትኩረት እንደሚያደርግ የተጠቆመ ሲሆን ወራቤ ዩኒቨርስቲ ለደቡብ ኮሪያው ዮንግናም ዩኒቨርስቲ ስልጠና መስጠት የሚያስችል ስምምነት መፈፀሙን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል፡፡

በቀጣይ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከዮንግናም ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የትምህርት ፕሮግራሞችን እንደሚከፍቱ በዩኒቨርስቲው የውጭ እና አለም አቀፍ ግንኑኙነት ሃላፊ እና በአካውንቲንግ ትምህርት ክፍል ረ/ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ማቲዎስ ከበደ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡በአሁን ሰዓት ስምምነቱን ተከትሎ ወራቤ ዩኒቨርስቲ ለደቡብ ኮሪያዉ ዮንግናም ዩኒቨርስቲ በአንዳንድ የትምህርት መስኮች በበይነ መረብ እና እንዲሁም በአካል ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ሃላፊው አስታውቀዋል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ ወራቤ ዩኒቨርስቲ ሀገራዊ የልማት አቅጣጫዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በግብርና እንዲሁም ደግሞ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ልምድ እና ተሞክሮዎችን እየወሰደ ይገኛል ሲሉ ዶ/ር ማቲዎስ ከበደ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *