(ክፍል-3)
👉 በዓለም ዋንጫው ውድ ተጫዋች ዝርዝር የፈረንሳዩ ኪሊያን ምባፔ በ160 ሚሊዮን ዩሮ ሲመራ፣ የብራዚሉ ቪንሽየስ ጁኒየር በ120 ሚሊዮን ዩሮ፣ፊል ፎደን፣ሞሳየላና ፔድሪ ተከታዮቹን ደረጃ ይዘዋል።
👉 የኳታር ዜጋ በመሆኑ ብቻ አንድ ሰው ኤሌክትሪክ ፣ ውሃ እና የጤና እንክብካቤ በነፃ ያገኛል።መንግስት የዜጎች ጡረታ የሚሸፍን ሲሆን ብድር ካስፈለጋቸው ያለ ማስያዣ ዜጎች የማግኘት መብት አላቸው።
👉 ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በመቀጠል ዝቅተኛ ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ኳታር ነች።
👉 ኳታር የአሜሪካ ግዛት ብትሆን ኖሮ ሶስተኛዋ ትንሹ ግዛት ትሆን ነበር።
👉 በጉዳት በውድድሩ የማናያቸው ተጫዋቾች መካከል ኒጎሎ ካንቴና ፖል ፖግባ እንዲሁም ካሪም ቤንዜማ(ከፈረንሳይ) ፣ማኔ(ሴኔጋል)፣ ዲያጎ ጆታ(ፖርቱጋል) ይጠቀሳሉ።
👉 ዛሬ በመክፈቻው ስነስርዓት ላይ የምንመለከታቸው የሀገሪቱ ኢምር ወይም መሪ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ የሚባሉ ሲሆኑ ከ2013 አንስቶሮ በስልጣን ላይ ይገኛሉ፡፡ የቤተሰቡ የሃብት መጠን ከ335 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል።
👉 ኳታር 0 የደን ሀብት በሚል የምትገለፅ ሲሆን የደን ሀብት የሌላት ሀገር ነች።
መልካም እድል ኳታር قطر حظا سعيدا
በስምኦን ደረጄ