መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 13፤2014-በዛሬዉ እለት ለገሀር የኢትዮ ቴሌኮም ጊቢ ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ 8 ቤቶች ጉዳት ደረሰባቸው

ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ 5:20 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለገሀር ኢትዮ ቴሌኮም መ/ቤት ጊቢ ዉስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ 8 ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማም ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ጉዳት የደረሰባቸዉ ቤቶች የኢትዮ ቴሌኮም መ/ቤት የጥበቃ ሰራተኞች መኖሪያ፣ የምግብ ማብሰያ፣መጋዘንና ካፌ ናቸዉ። የአደጋ ጥሪዉ እንደደረሰዉ ከቂርቆስና ከአራዳ ቅርንጫፍ መ/ቤት አምስት የአደጋ መቆጣጠር ማሽነሪዎች ከበቂ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ማሰማራቱ ተጠቁሟል፡፡

እሳቱን ለማጥፋት በተደረገ ርብርብም እሳቱ በርካታ አገልግሎት ወደ ሚሰጥባቸዉ ህንጻ እንዳይዛመት ማድረግ ተችሏል። በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን በአደጋዉ የወደመ ንብረት ግምትና የአደጋዉ መንስኤ እየተጣራ ይገኛል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *