መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 13፤2014-ናይጄሪያዊው ባል ሚስቱን በረሃብ በመቅጣቱ ተከሰሰ

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የዮቤ ግዛት ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ባለቤቱን ያለ ምግብ ለረጅም ጊዜ በማስቀመጥ ለሞት ዳርጓል በተባለዉ ግለሰብ ሁኔታን እያጣራ መሆኑን አስታዉቋል።ተጎጂዋ በእረፍ ቀናቱ በካኖ በሚገኝ ሆስፒታል ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በዮቤ ግዛት ከሚገኘዉ የጥንዶቹ መኖሪያ ቤት በሰዎች እርዳታ ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም ህይወቷን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

የግዛቲቱ የፖሊስ ቃል አቀባይ ዱንጉስ አብዱልከሪም እንደተናገሩት ባልየው በቁጥጥር ስር መዋሉን በመግለጽ ምርመራው እንደተጠናቀቀ ለፍርድ እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡የአራት ልጆች እናት የነበረችውን ተጎጂዋን ጤናማ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ እንድትቆይ እና ምግብ በጠየቀች ጊዜ ሁሉ “ኩኑ” የሚባል የአካባቢውን መጠጥ ብቻ እያቀረበላት ነበር የሚል ክስ ቀርቦበታል። ባል ግን ክሱን አስተባብሏል፡፡

ባል ወደ ሚስቱ ክፍል ማንም እንዳይገባ የከለከለ ሲሆን ሁኔታዉን እንደተረዱ የሟች እናት ጉዳዩ ወደ አደባባይ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡የሴቲቱ ህልፈት ህዝባዊ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን የሴቶች መብት ተሟጋች ቡድኖች ፍትህ እንዲሰጥ ቅስቀሳ ጀምረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *