መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 13፤2014-🇶🇦አጫጭር መረጃዎች በኳታርና በዓለም ዋንጫ ዙሪያ


(ክፍል -4)

👉 የአለም ዋንጫ ኳሶች ፍጥነት ጨምሯል ሲል የኡራጓይ ግብ ጠባቂ ተናግሯል።የኡራጓያዊው ግብ ጠባቂ ሰርጂዮ ሮቼት እንደተናገረው ከዓመት አመት ኳሱ ለአጥቂዎች የተሻለ ይሆናል ለእኛ ለግብ ጠባቂዎች ግን በጣም ከባድ እየሆነ መጥቷል ሲል ተናግሯል።

👉 በትውልድ ሀገሩ ለሚገኘው ክለብ ናሲዮናል የሚጫወተው የ29 አመቱ ተጫዋች የአሰልጣኝ ዲያጎ አሎንሶ የመጀመሪያ ምርጫ ነው።ብሄራዊ በድኑ ለአራት ጊዜ በአለም ዋንጫው የሚሳተፉትን እንደ ሉዊስ ሱዋሬዝ እና ኤዲሰን ካቫኒ ጨምሮ በወጣቶች የተዋቀረ ነው።

👉 አል ሪህላ ወይም በአረብኛ ‘ጉዞው’ የሚል ስያሜ የተሰጠው ኳስ በዓለም ዋንጫ ውድድር ታሪክ ውስጥ ከየትኛውም ኳስ በበለጠ በፍጥነት ይጓዛል።

👉 የመጫወቻ ሜዳ ሳሩ ለምለም እና አረንጓዴ ሆኖ ለማቆየ በየቀኑ 10,000 ሊትር ጨዋማ ያልሆነ ውሃ ኳታር ጥቅም ላይ እያዋለች ነው።

👉 22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ በ32 ቡድኖች መካከል የሚደረግ ውድድር ይሆናል። የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ በ1930 በኡራጓይ ሲካሄድ 13 ቡድኖች ብቻ ተሳትፈዋል።

👉 በ1934 ወደ 16 ቡድኖች ከፍ ያለ ሲሆን በ 1982 ወደ 24 ቡድኖች በማደግ በ 1998 አሁን ያለው ቅርጸት ላይ ደርሷል።

👉 በሚቀጥለው 23ኛው የዓለም ዋንጫ በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ ሲያዘጋጁት 48 ቡድኖች ይኖሩታል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *