መደበኛ ያልሆነ

ጥር 15፤2015-በደሴ ዙሪያ ወረዳ ባልተለመደ መልኩ ሶስት ቀንዶች ያሉት በግ አነጋጋሪ ሆኗል

በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ዙሪያ ወረዳ 032 አስጎሪ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ባልተለመደ መልኩ ሶስት ቀንዶች ያሉት በግ መነጋጋሪያ ሆኗል፡፡

የበጉ ሶስተኛ ቀንድ በግንባሩ ላይ የሚገኝ ሲሆን በግራ እና በቀኝ በኩል ከሚገኙ ቀንዶቹ እንደሚለይ ተገልጿል ። በጉ ከሌሎች በጎች የተለየ ባህሪ እንዳለው እና ሰው ሲቀርበው እንደሚበረግ የደሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አ/ቶ ጀማል ሙሃመድ ለብስራት ሬዲዮ ተናግሯል ።

ከተለመደው የበግ ሁለት ቀንድ በተለየ ሁኔታ ሶስት ቀንድ ያሉት ይኸው በግ አውራ በግ እንደሆነ ተገልጿል ። ሶስተኛ በመሆን በግንባሩ ላይ በመብቀል ያደገው ቀንድ ቀጥ ያለ መሆኑን አቶ ጀማል ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *