መደበኛ ያልሆነ

ጥር 15፤2015-የዛምቢያ ፕሬዝዳንት የትዳር አጋራችሁን ስልክ መሰለሉን አቁሙ ፍቺ የጨመረዉ ለዚህ ነዉ ሲሉ ምክር ለገሱ

የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ የሀገሬ ሰዎች የትዳር ጓደኞቻችሁን ስልክ መሰለል እንድታቆሙ አሳስባለዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡በዛምቢያ ያለዉ የፍቺ መጠን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ ይህንን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በዛምቢያ ባለፈው አመት ብቻ ከ22,000 በላይ ፍቺ መመዝገቡን ፕሬዝዳንቱ አሀዛዊ መረጃ ጠቅሰዉ ተናግረዋል፡፡በጋብቻ ዉስጥ የመብት እጦት፣ በትዳር ላይ መደረብ፣ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ ስድብ እና ጭካኔ ሰዎች በፍርድ ቤት ለፍቺ ከሚጠቅሷቸዉ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ናቸው።

“የምንጋባው ለፍቅር ነው፣ ሄደን ለመፈተሽ ወይም ጣት ለመቀሰር አይደለም” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሂቺሌማ ከዛምቢያ ባህላዊ ንጉሰ ነገስት ጋር በነበነራቸዉ ቆይታ ተናግረዋል፡፡አክለውም “ነጻነት ማለት ነፃነታችንን የመገደብ ሃላፊነት እንጂ የሌሎችን ነፃነት መንካት አይደለም፤ ታጋሽ ሁኑ፣ ሌሎችን ተረዱ” ሲሉ አክለዋል፡፡

ባለፉት 12 ወራት የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዛምቢያ አጭሩ ጋብቻ ለ 30 ቀናት የቆየ ሲሆን ረጅሙ ደግሞ 65 ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *