መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 16፤2015-በኢትዮጵያ የህጻናት የካንሰር ስፔሻሊስት ሃኪሞች ብዛት ስምንት ብቻ መሆናቸዉ ተነገረ

በኢትዮጵያ በህጻናት የካንሰር ህክምና አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሃኪሞች ቁጥር ስምንት ብቻ መሆናቸውን የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሆስፒታል አስታዉቋል፡፡በሆስፒታሉ የህጻናት የደምና የካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪም የሆኑት ዶክተር ማሙዴ ድንቅዬ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የህፃናት ካንሰርን አስቀድሞ ለመከላከል በሽታው ቶሎ ከተገኘና ህክምናው በጊዜው ከተጀመረ  የመዳን እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ እንደ ሃገር በዚህ የህክምና ዘርፍ ያሉት የሃኪሞች ቁጥር ከስምንት ያልበለጡ መሆናቸውን ተከትሎ  በርካታ ህጻናት በቂ ህክምናን እንዳያገኙና  የመዳን እድላቸው ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡ይህም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የካንሰር ህክምና አገልግሎት ሽፋንን ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል ያሉት የህክምና ባለሙያው ችግሩን ለመቅረፍ አዳዲስ የህክምና ባለሙያዎች በዘርፉ እንዲሰማሩ ማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አያይዘውም በዘርፉ ያለውን የህክምና ባለሙያዎች እጥረትን ለማስወገድ ቀጣይነት ያላቸው ስልጠናዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ስፍራዎች በሚገኙ ከፍተኛ  የትምህርት ተቋማት እየተሰጡ ይገኛሉ ሲሉ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በቅድስት ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *