???? አሜሪካ በሩሲያ ላይ ወረራ እንዲፈፀም አላበረታታም ብላለች
ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ ላይ የተፈፀመውን ወታደራዉ ወረራ ተከትሎ እጄ የለበትም ስትል ከጉዳዬ ራሷን አግላለች። ሞስኮ ከዩክሬን በገቡት የታጠቁ አማፂያንን መውጋቷን ገልፃለች።
ባለፈው አመት ከተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ወዲህ ከሩሲያ ዋና ዋና የድንበር አቋራጭ በሆነው የቤልጎሮድ የድንበር አካባቢ ክፍሎች ላይ ሰኞ እለት ጥቃት ደርሷል። ሩሲያ የወደሙና የተበላሹ ንብረትነታቸው የምዕራባውያኑ ሀገራት የሆኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ምስሎችን አጋርታለች፤ ከእነዚህም መካከል አሜሪካ ሰራሽ ሃምቪስን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ይፋ ተደርገዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ “በሩሲያ ላይ ጥቃት እንዲፈፀም አላበረታታም ” ስትል ግን አስታውቃለች። የአሜሪካ መንግስት ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ዩናይትድ ስቴትስ ሰራች የጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን “በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎችም ቦታዎች እየተሰራጩ ያሉ” ዘገባዎች መኖራቸውን አምኗል።ነገር ግን ሀገራቸው “የእነዚህ ዘገባዎች ትክክለኛነት በዚህ ጊዜ ተጠራጣሪ ነች” ብሏል።
“ይህን ጦርነት እንዴት መምራት እንዳለባት የመወሰን ጉዳት የዩክሬን ነው” ሲል አክሏል። በድንበር አቅራቢያ የሚገኙ የቤልጎሮድ መንደር ነዋሪዎች በተፈጠረው ተኩስ ከአካባቢው ተፈናቅለዋል። ሩሲያ ወረራ የፈፀሙብኝን 70 ታጣቂዎችን ገድያለው ስትል ገልጻለች። ነገር ግን ዩክሬን የሩሲያ ምድር ላይ ወረራ እንዳልፈፀመች ተናግራለች።
በሌላ በኩል የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን የሚቃወሙ ሁለት የሩሲያ ታጣቂ ቡድኖች ወረራውን የፈፀምነው እኛ ነን ሲሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል ። በሩሲያ ላይ የተፈፀመውን ወረራ ተከትሎ የሞስኮ መንግስት በሽብርተኝነት ላይ ዘመቻ መክፈቱን አውጇል። ይህንኑ ተከትሎ የፀጥታና የደህንነት ባለስልጣናት የመገናኛ እና የህዝብ እንቅስቃሴን ለመግታት ልዩ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ከወሰዱና የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተቃዋሚ ቡድኖች መካከል አንዱ አሁንም ” የራሳችንን የእናት ሀገር ቁራጭ ግዛት” ተቆጣጥሬያለሁ ሲል ተናግሯል። የቤልጎሮድ ገዥ በግጭቱ ወቅት አንድ ሲቪል ሰው መሞቱን እና ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል ብለዋል።
ገዢው ቫያቸስላቭ ግላድኮቭ ማክሰኞ ማምሻውን እንደተናገሩት ቤልጎሮድ ከሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ የተጣለ ፈንጂ በመኪና ላይ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።
በስምኦን ደረጄ