መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 17፤2015-የጦር መሣሪያዎችን ለሩሲያ አቀርባለሁ ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ታዋቂዉ ፖለቲከኛ ጁሊየስ ማሌማ ተናገሩ

የደቡብ አፍሪካ ሶስተኛው ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ የሆነዉ የኢኮኖሚ ነፃነት ተዋጊዎች መሪ “ሞስኮ ከኢምፔሪያሊዝም ጋር ጦርነት ውስጥ ስለገባች “ለሩሲያ የጦር መሳሪን አቀርባለዉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ጁሊየስ ማሌማ በጆሃንስበርግ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ደቡብ አፍሪካ የሩስያ አጋር ናት” በማለት እና የደቡብ አፍሪካ ገዢ መንግስት ያለመስማማት አቋም በዩክሬን ጦርነት ላይ ብቻ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል።

“ከሩሲያ ጋር ከጓደኝነት በላይ አልፌ እሄዳለሁ፤ በጦርነቱ ውስጥ ከሩሲያ ጋር እስማማለሁ እና መሳሪያዎቹን እንኳን አቀርባለሁ”ሲሉ ማሌማ ተናግረዋል፡፡ደቡብ አፍሪካ ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) እንድትወጣ እንደሚፈልጉም አክለዋል።

አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) በቭላድሚር ፑቲን ላይ በጦር ወንጀለኝነት ክስ የእስር ማዘዣ አውጥቷል፡፡ ነገር ግን ማሌማ በሚቀጥለው ወር በኬፕታውን በሚካሄደው የብሪክስ ሀገራት ስብሰባ ላይ ፑቲን ከተገኙ እሳቸዉን ለመያዝ የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ ለመከላከል ቃል ገብተዋል ።ማሌማ አስተያየታቸውን የሰጡት በደቡብ አፍሪካ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ባለፈው ታህሳስ ወር ደቡብ አፍሪካ የሩሲያ መርከብ ላይ የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች ጭናለች በሚል ክስ ከመሰረቱና ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት መፈጠሩን ተከትሎ ነው።

የደቡብ አፍሪካ መንግስት ወደ ሩሲያ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ እንዲላክ አልፈቅድም በማለት የአሜሪካን ክስ ማስተባበሉ ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *