መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 6፤2015-በማዕከላዊ ዩክሬን በሚገኝ ባለ 5 ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ ሩሲያ የአየር ላይ ጥቃት ፈፀመች

ሩስያ በማዕከላዊ ዩክሬን ክሪቪ ሪህ ከተማ ባለ አምስት ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃን ጨምሮ የሲቪል ተቋማት ላይ ኢላማ ያደረጉ የአየር ጥቃቶችን መሰንዘሯን ተከትሎ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ነዋሪዎችን ከፍርስራሹ ውስጥ ማትረፍ መቻሉን የአከባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። ዛሬ ማለዳ ላይ በቴሌግራም የመልእክት ማጋሪያ መተግበሪያ የከተማዋ ከንቲባ ኦሌክሳንደር ቪልኩል “በጣም ከባድ በሆነ ሁኔታ የቆሰሉ ሰዎች አሉ” ሲሉ ገልፀዋል ።

ምናልባት ከፍርስራሹ ስር በህይወት ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ሲሉም አክለዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጩ የቪዲዮ ምስሎች መሰረት በከተማዋ ጥቃት ሲሰነዘር እና የወደማ የመኖሪያ አፓርትመንቶች እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎዎችን አመላክተዋል። ዋና ከተማዋ ኪየቭ ማክሰኞ ማለዳ ላይ የአየር ጥቃት ደርሶባታል ነገርግን የአየር ጥቃት መቃወሚያ ዘዴዎች ወደ ከተማዋ የተወነጨፉትን ሚሳኤሎች በሙሉ አወደሙ ሲሉ የወታደራዊ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የኪየቭ ከተማ የጦር ክፍል መሪ የሆኑት ሰርሂይ ፖፕኮ በሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት እና ስለ ንብረት ውድመት ምንም መረጃ እስካሁን አልደረሰንም ሲሉ ተናግረዋል።በምስራቅ ዩክሬን በካርኪቭ ክልል ላይ በተመሳሳይ ሩሲያ ጥቃት መፈጸሟ ተዘግቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *