መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 7፤2015-በናይጄሪያ ከሰርግ ስነ ስርዓት ሲመለሱ የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች በጀልባ አደጋ ህይወታቸዉ አለፈ

በደቡብ ምእራብ ናይጄሪያ በኒጀር ወንዝ ላይ መንገደኞችን ያሳፈረች ጀልባ ተገልብጣ ከ100 በላይ ሰዎች ሰጥመው የደረሱበት እንዳልታወቀ የናይጄሪያ መንግስት ባለስልጣናት ገልጸዋል።ጀልባዋ ከ300 በላይ መንገደኞችን አሳፍራ ከኳራ ግዛት ወደ ኒጀር ግዛት ከሠርግ ሥነ ሥርዓት የሚመለሱ ሰዎችን አሳፍራ ነበር።

ተጨማሪ ተጎጂዎችን ለማግኘት የማፈላለግና የማዳን ስራ ቀጥሏል ሲሉ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።ጀልባዋ ከዛፍ ጋር ከተጋጨች በኋላ ተገልብጣለች ሲሉ የአካባቢው ባህላዊ አስተዳዳሪ ተናግረዋል።የኳራ ግዛት ገዥ አብዱራህማን አብዱልራዛቅ በሰጡት መግለጫ “100 ያህል ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል እና ሌሎች ደግሞ ጠፍተዋል” ሲሉ ተናግረዋል ።

የፓቲጊ ሲሚር ኢብራሂም ኡመር ቦሎጊ ሁለተኛ በአካባቢው ባህላዊ አስተዳዳሪ ሲሆን ከ 150 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን እንዳጡ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ከዛፉ ጋር ጀልባዋ መጋጨቷን ተከትሎ በዉሃ በማጥለቅለቅ ጀልባዋ እንድትገለበጥ አድርጓታል።የኳራ ግዛት ፖሊስ ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡የኳራ ግዛት ገዥ አብዱልራዛቅ ለተጎጂዎቹ ወዳጅ ዘመዶቻቸው “ልባዊ ሀዘናቸውን” በመግለጽ የነፍስ አድን ጥረቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *