መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 7፤2015-ዉዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ጀርባ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ እድሜዉ 35 ዓመት የተገመተ ሰዉ ህይወቱ አልፎ ተገኘ

በአዲስ አበባ ከተማ ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ዉዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ጀርባ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ እድሜዉ 35 ዓመት የተገመተ ሰዉ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን ከወንዝ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

በሌላ ዜና ሰኔ 6 ቀን 9 ሰዓት አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ሁለት የንግድ ሱቆች የተቃጠሉ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ እሳት ሳይዛመት መቆጣጠር ተችሏል ።

በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለ።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *