መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2015-ብሊንከን የአሜሪካንና የቤጂንግ የሻከረ ግንኙነት ለማደስ ቻይና ይገኛሉ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሁለቱ ኃያላን ሀገራት መካከል ያለውን የግንኙነት መበላሸት ለማሻሻል በትላንትናው እለት ወደ ቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ገብተዋል። በየካቲት ወር ቻይናን ለመጎብኘት አቅደው የነበረ ቢሆንም በአሜሪካ የአየር ክልል ላይ የቻይና ነው የተባለው የስለላ ፊኛ በዋሽንግትን በጥይት መመታቷን ተከትሎ ጉዞውን ለሌላ ጊዜ እንዲተላልፍ አስገድዷል።

አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ከአምስት ዓመታት ገደማ በኋላ ቻይናን ሲጎበኙ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው። ብሊንከን ከቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ ጋር መምከራቻው ተሰምቷል።ከፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር እንደሚገናኙ እስካሁን ግልፅ አይደለም።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰብዓዊ መብቶች እና በታይዋን ላይ በተከሰቱ ግጭቶች እና ውጥረቶች ምክንያት የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መጥቷል ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *