መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 13፤2015-በኢትዮጵያ የተቋረጠዉ የምግብ እርዳታ በሃምሌ ወር ዳግም እንደሚጀምር ተሰማ

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በትግራይ ያቋረጠውን የምግብ እርዳታ ስርጭት በመጪው ሃምሌ ወር ለመጀመር እቅድ መያዙን አስታውቋል።

ድርጅቱ የእርዳታው ተጠቃሚዎች በምን መልኩ እንደሚመረጡ ከፍተኛ ቁጥጥር ካደረገ በኋላ በሚቀጥለው ወር የምግብ ዕርዳታ ስርጭቱን ዳግም ለመጀመር ማቀዱ ተሰምቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አንድ ባለስልጣን እንገለጹት “የአለም ምግብ ፕሮግራም የእርዳታው ተጠቃሚዎችን በመምረጥ ሂደት ውስጥ የበለጠ ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊኖረው ይገባል “ያሉ ሲሆን፤ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት አዉንታዊ ግብረ መልስ ከተገኘ በኋላ፤ በትግራይ እና ለስደተኞች ካምፖች የሚያርገውን እርዳታ በሃምሌ ወር አጋማሽ ላይ ሊቀጥል እንደሚችል ገልጸዋል።

ድርጅቱ በትግራይ ክልል በግንቦት ወር በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ደግሞ በሰኔ ወር “የእርዳታ እህል ስርቆት ተበራክቷል” በሚል ምክንያት የምግብ ድጋፉን ማቋረጡ ይታወሳል። በምስራቅ አፍሪካ አስከፊ በተባለዉ ረሃብ በኢትዮጵያ ብቻ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ድርጅቱ አስታዉቋል።

ለዚህም ምክንያቱ በቀጠናዉ ባለፉት አስርት ዓመታት የተከሰተው አስከፊ ድርቅ እና በትግራይ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት መሆኑ ተመላክቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከእነዚህ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ውስጥ፤ ወደ 6 ሚሊዮን ለሚጠጉ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ሲሰጥ መቆየቱንም ባለስልጣኑ ገልጸዋል። የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡ ለህጻናት ፣ ነፍሰጡር እና ጡት ለሚያጠቡ እናቶቸ የሚደረገዉን የተሰመጣጠነ የምግብ ድጋፍ እንደማይመለከትም ተሰምቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *