መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 13፤2015-በወላይታ ዞን በሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ ያልተፈቀዱ ተግባራት ሲፈፅሙ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በወላይታ ዞን ሰኔ 12 ቀን የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ በሰላም መጠናቀቁ ተገልፆል፡፡በምርጫ ሂደቱ ላይ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በምርጫው ቀን አንድ ግለሰብ ሀሰተኛ መታወቂያ ተጠቅሞ ለመምረጥ የሞከረ እና ሁለተኛው ደግሞ የምርጫ ቦርድ ባጅ ይዞ በመገኘቱ እያንዳንዳቸው በ6 ወር እስራት እንዲቀጠ ተወስኖባቸዋል፡፡

በተጨማሪም የተለየ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያድጉ የነበሩ 7 ግለሶች በቁጥጥር ስር ውለው የፍርድ ቤት ሂደታቸው በመጣራት ላይ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *