መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 14፤2015-በሹፌሩ የተሰረቀ ደብል ፒካፕ መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ

ከአፋር ክልል በአሽከርካሪው የተሰረቀ የመንገድ ስራ ድርጅት ተሽከርካሪ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ እሮቢት ከተማ ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል ።

ንብረትነቱ የሻንድንግሉቸው ማንዳ ቡሬ መንገድ ስራ ድርጅት የሆነ የሰሌዳ ቁጥር አ.አ B 14630 ደብል ፒካፕ ቲዮታ መኪና ሲሆን መነሻውን ከአፋር ክልል  አንድ ኤሊዳር ወረዳ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል ።

አሽከርካሪው በፀጥታ ሀይል ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ተረድቶ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ እሮቢት ከተማ መኪናውን አቁሞ የተሰወረ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ተመስገን በረሳው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

መኪናው የተሰረቀው በድርጅቱ ሾፌር በሆነ አለም በሪሁን በተባለ ግለሰብ መሆኑንና ሌላ የድርጅቱን መኪና ከተመለከተ በኋላ መኪናውን አዙሮ እሮቢት ከተማ መመለሱ ተነግሯል ።  ነገር ግን ሌላኛው የድርጅቱ መኪና በአካባቢው ለስራ በጉዞ ላይ የነበረ እንደሆነ ተገልጿል ።

ተሽከርካሪውን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ባለንብረት ለሆነው ድርጅት በትናንትናው ዕለት ያስረከበ መሆኑንና ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *