መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 14፤2015-ባይደን የቻይናን መሪ ዢን አምባገነን ናቸው ሲሉ ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በካሊፎርኒያ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በመገኘት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አምባገነን ናቸው ሲሉ ጠርተዋል።የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከፕሬዝዳብት ዢ ጋር በቤጂንግ ተገናኝተው ከመከሩ ከአንድ ቀን በኋላ ይህንኑ ንግግር ባይደን የተናገሩ ሲሆን በሁለቱ ኃያላን ሀገራት መካከል ያለውን አለመግባባት ለማርገብ የተደረገው ጥረት ላይ ቤንዚን እንደመጨመር ተደርጎ ተወስዷል።

ዢ በቤጂንግ አንዳንድ መሻሻሎች ታይተዋል ሲሉ በአሜሪካ ቻይና ግንኙነት ዙሪያ የተናገሩ ሲሆን ብሊንከን ግን ሁለቱም ወገኖች ለተጨማሪ ንግግሮች ክፍት መሆናቸውን ጠቁመዋል። ቻይና ለባይደን ንግግር እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም። ፕሬዝዳንት ባይደን፣ ማክሰኞ ምሽት በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ፣ ዢ በቅርቡ በአሜሪካ ግዛት ላይ የቻይና የስለላ ፊኛ ዙሪያ በተፈጠረው ውጥረት ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።

“ዢ ጂንፒንግ በጣም የተናደዱበት ምክንያት፣ ያንን የስለላ ፊኛ በሁለት ቦክስ መኪኖች የሞሉ የስለላ መሳሪያዎች መትተ በጣልን ጊዜ፣ ዢ ምን እየተደረገ  እንዳለ ስላላወቁ ነው” ብለዋል ። “ይህ ለአምባገነኖች በጣም አሳፋሪ ነው ምን እንደተፈጠረ ሳያውቁ ሲቀሩ” ሲሉ አክለዋል። ብሊንከን በቤጂንግ ጉብኝት ሲያደርጉ ከአምስት ዓመታት ገደማ በኋላ በአንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት የመጀመሪያው ።

ዋሽንግተን እና ቤጂንግ በንግድ፣ በሰብአዊ መብትን እና ታይዋንን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለረዥም ጊዜ ሲወዛገቡ ቆይተዋል። ይህው የሻከረ ግንኙነቱ በተለይ ባለፈው ዓመት ተባብሷል። የአሜሪካ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት በዙህ ወቅት ከቻይና ጋር ያለው ውጥረት እንደ ፖለቲካ ጉዳይ ብቅ እያለ ሲሆን አንዳንድ የሪፐብሊካን ሴናተሮች የባይደንን አስተዳደርን በቻይና ላይ “ለስላሳ” በማለት ጥቃት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *