መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 16፤2015-በአሶሳ ከተማ ያጋጠመውን የሽንኩርት እጥረት ለመፍታት ከሱዳን እየገባ እንደሚገኝ ተነገረ

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከሳምንታት በፊት በተከሰተ የሽንኩርት እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቶ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ገበያውን ለማረጋጋት በተሰራ የንግድ ትስስር ከሱዳን የሽንኩርት ምርት እየገባ እንደሚገኝ ተነግሯል ።

የሽንኩርት ምርትን ነጋዴዎች ከጉምሩክ እና ከክልሉ ንግድ ቢሮ ባገኙት ፈቃድ መሰረት ከሱዳን እያስገቡ እንደሚገኝ ተገልጿል ። በአሁኑ ወቅት ሽንኩረት በኪሎ ጅምላ በ68 ብር ሲሸጥ በችርቻሮ 70 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ በከተማ አስተዳደሩ የወረዳ ሁለት ንግድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አ/ቶ ወሊድ አንዋር ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

በተጨማሪ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በቂ ባልሆኑ ምክንያቶች የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላትን እና ህገወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ የድርጊቱን ፈጻሚዎች በመጠቆም መተባበር እንደሚገባ አ/ቶ ወሊድ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *