መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 19፤2015-በታሪክ ትልቁ የሃጅ ጉዞ በሳውዲ አረቢያ ተጀመረ

ነጭ ልብስ የለበሱ ሙስሊሞች በእስልምና ቅዱስ በሆነው ስፍራ በመገኘት የሐጅ ጉዞ ተጀመሯል። አመታዊ የሐጅ ስነስርአት እሁድ እለት በመካ ሳውዲ አረቢያ በካዕባ መጀመሩን የሳዐዲ አረቢያ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የሳውዲ የሃጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ባለስልጣን “በዚህ አመት በታሪክ ትልቁን የሃጅ ጉዞ መሆኑን ምስክር ነን” ብለዋል ።

ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በ2020 ዓመት በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ10,000 ያህል ሰዎች ብቻ እንዲሳተፉ ተፈቅዶላቸው እንደነበር ይታወሳል።በ 2021 ዓመት ደግሞ 59 ሺ ሰዎች ተሳትፈዋል። ባለፈው ዓመት አንድ ሚሊዮን ሰዎች መገኘታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

6000 ዶላር በመክፈል ለ20 አመታት ያጠራቀመው የ65 አመቱ ግብፃዊ አብዱላዚም “በህይወቴ ውስጥ እጅግ ውብ የሆኑትን ቀናት እያሳለፍኩ ነው” ሲል በቦታው ላይ በመገኘት ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዜና አገልግሎት ተናግሯል።

ወደ 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚጠጋው ሙቀት የጤና ችግር እንዳያስከትል ሳዑዲ አረቢያ መዘጋጀቷን አስታውቃለች።የሳዑዲ ባለስልጣናት እንዳሉት ከ32,000 በላይ የጤና ባለሙያዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ አምቡላንሶች በሙቀት የሚፈጠረውን መጨናነቅ እና የድካም ስሜትን ለማከም በተጠንቀቅ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *