መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 19፤2015-በአዲስ አበባ ከተማ ትቦ ዉስጥ ተጥሏል ተብሎ በስካቫተር ሲፈለግ የነበረው የጨቅላ ህጻን ድምጽ የአምስት ቡችሎች ሆኖ ተገኘ

በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ከቀኑ 9:30 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 መሳለሚያ ሸዋ ጸጋ ገበያ ማዕከል ፊት ለፊት ነው። በስፍራው የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦ ዉስጥ  የጨቅላ ህጻን ድምጽ መስማታቸዉን ተከትሎ የአካባቢዉ ህብረተሰብ ለእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መደወላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቃል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና መረጃዉ የደረሰዉ ፖሊስ በስፍራው ላይ መድረሱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከትቦዉ ዉስጥ እየሰሙ ያለውን  ድምጽ ተከትለዉ በእስካቫተር ማሽን ታግዘዉ እየጣለ የነበረዉ ከባድ ዝናብ ህጻኑን በጎርፍ እንዳይወሰድ በከፍተኛ ፍጥነትና ጥንቃቄ ድምጽ የሚሰማበትን ጆንያ ከጉድጓዱ ወስጥ አዉጥተዉታል።

በርካታ ሰዎች  የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ፖሊሶች ህጻን በጆንያ ተጠቅልሎ ተጥሎ ነዉ የሚል ጥርጣሬ ቢኖርም ከትቦ ዉስጥ የተገኘዉ ህጻን ልጅ ሳይሆን በጆንያ የተጠቀለሉ አምስት ጨቅላ ቡችሎች ሆነዉ መገኘታቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ወደ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያደረገው ወጣት በየግዜው ጨቅላ ሕፃናት በትቦ እና በመፀዳጃ ቤት ተጥለው መገኘታቸው መረጃ ስለሚሰማ ከጉድጓድ ውጥ የሰማው ድምፅ የተጣለ ሕፃን ነው የሚል እርግጠኝነት እንደነበረው አስታወቋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *