???? በዛሬው እለት ብቻ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል
በኦሮሚያ ክልል ከግንቦት 12 እስከ ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መረጃ ጥናት እና አገልግሎት ዲቪዥን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
አደጋዎቹ በደቡብ ምእራብ ሸዋ ወሊሶ፣ምስራቅ ሀረርጌ ግራዋ ፣በምእራብ አርሲ ጅራሮ ወረዳዎች እና ባቱ ፣አሰላ፣አዳማ እና አንቦ ከተማዎች የደረሱ ናቸው።አደጋዎቹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ለሊቱ 11:00 ሰዓት ተመዘገቡ ናቸው።
የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት ተሽከርካሪ፣ በህዝብ ማመላለሻ እና በባለ ሶስት እግር እና በሞተር ሳይክል ተሸርከርካሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡።የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የጨመረ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም