መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 22፤2015-ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ስራ ካቆመ ሶስት ወራት ማስቆጠሩ ተገለጸ

በአዲስአበባ የሚገኘዉ ከቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጨው ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ስራ ካቆመ ሶስት ወራት ማስቆጠሩን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 26ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ። ለዚህም ተቋሙ ከኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የሚደረግለት ክትትልና ድጋፍ የሌለ መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዉ በሰዓት 50 ሜጋ ዋት ለማመንጨት የተቋቋመ የነበረ ቢሆንም ከሶስት ወራት በፊት መስሪያቤቱ ባደረገዉ ክትትል 13 ሜጋ ዋት ብቻ እያመነጨ የነበረ መሆኑን ጨምረዉ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ባለስልጣኑ ዉፍረታቸዉ 0.03 ሚሊ ሜትር እና ከዚያ በታች የሆኑና ከአፈር ጋር በቀላሉ የማይቀላቀሉና የማይበሰብሱ ምርቶችን ተለይቶ ከተቀመጠው አገልግሎት በቀር ወደ ሀገር እንዳይገቡ ወይም እንዳይመረቱ ተከታታይነት ባለዉ መልኩ ክትትል ማድረግ ሲገባዉ ይህን ያለከናወነ መሆኑ ፤ ከህግ ዉጪ የሰሩ ተቋማትንም እርምጃ እንዲወሰድባቸው ያላደረገ እንዲሁም በርካታ ሀላፊነቶቹን ያልተወጣ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ፊት ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *