መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 26፤2015-በህገ ወጥ መንገድ በተከማቸ ቤንዚል በተነሳ የእሳት አደጋ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ

በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ አስተዳደር ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ላይ በአንድ ግለሰብ ሱቅ ዉስጥ በህገ ወጥ መንገድ ባለሁለት ሊትር ሃይላንድ ለሽያጭ የተከማቸ ቤንዝን  ከእሳት ጋር በመገናኘቱ በደረሰው አደጋ አራት መኖሪያ ቤቶች እና አንድ መጋዘን ከነሙሉ ቁሳቁስ መዉደሙ ተገልጿል።

የእሳት አደጋዉ የተነሳዉ ተከራዮች ዉጪ ላይ ከሰል እያቀጣጠሉ በንፋስ አማካኝነት ለሽያጭ ናፍጣ እየተቀዳ ካለዉ ጋር በመያያዙ እሳቱ መነሳቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽኑ  ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

በቃጠሎዉ የአራት ግለሰቦች መኖሪያ ቤት፣ መጋዘን በቃጠሎዉ ሙሉ በሙሉና በከፊል የወደመ ሲሆን እሳቱ ሳይዛመት የአከባቢዉ ነዋሪዎችና ፖሊስ ተረባርበዉ እሳቱን የጠፋ ሲሆን በቃጠሎ  ከ2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

በከተማዉ የነዳጅ ማደያ ባለመኖሩ ህብረተሰቡ ቤንዝል በጀሪካን እና በውሃ መያዣ  ጥንቃቄ በጎደለዉ መንገድ ለሽያጭና ለተለያዩ አገልግሎቶች እንደሚያዉሉ ይህም ለቃጠሎ መንስኤ ነዉ ሲሉ ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *