መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 27፤2015-በእስር ላይ የሚገኘዉ የጋዳፊ ልጅ ሃኒባል በአስጊ የጤና ሁኔታ ላይ መሆኑ ተነገረ

በህይወት ካሉት የሊቢያዉ የቀድሞ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጆች መካከል አንዱ የሆነዉ ሃኒባል ጋዳፊ የረሃብ አድማ ላይ ከነበረበት የሊባኖስ እስር ቤት “በአስከፊ ሁኔታ” ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተዘግቧል።

የሮይተርስ የዜና ወኪል በዱባይ የሚገኘውን አል-ሃዳት ቲቪን ጠቅሶ እንደዘገበው በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ዘግቧል።ሃኒባል ጋዳፊ በሊባኖስ ከስምንት ዓመታት በላይ በእስር ላይ ይገኛል።

ያለ ፍርድ ቤት ለረጅም ጊዜ መታሰሩን በመቃወም ባለፈው ወር የረሃብ አድማ አድርጓል፡፡እ.ኤ.አ. በ 2011 ወላጅ አባቱ ጋዳፊ በአማፂያን ከተገደሉ በኋላ ወደ ሶሪያ የሸሸ ቢሆንም እጁ ከተያዘበት ጊዜ አንስቶ በሊባኖስ በእስር ላይ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *