መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 29፤2015-በሁሉም ባንኮች በቁጠባ የተሰበሰበው ገንዘብ 2.1 ትሪሊዮን መድረሱን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ያሉ የባንኮች ቁጥር 31 መድረሱን ተናግረዋል። የመንግስታቸዉ ለዉጥ አንዱ የሆነዉ የኢኮኖሚያዊ መሻሻል ማሳየት መቻሉ መሆኑን የተለያዩ ማጣቀሻዎችን አንስተዉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት የባንኮችን ቁጥር ከፍ ከማድረግ በዘለለ በሁሉም ባንኮች በቁጠባ የተሰበሰበው ገንዘብ መጠን 2.1 ትሪሊዮን መሻገሩን ገልጸዋል። ከዚህ ዉስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ መጠን ብቻ ከ 1 ትሪሊዮን ብር በላይ መሻገሩን ብስራት ራዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

በተጨማሪም 100 ሚሊዮን የቁጠባ ሂሳብ  መከፈቱንም አክለዋል። በሌላ በኩል  የባንኮችን ቅርንጫፎች ተደራሽ ከማድረግ አኳያ 11 ሺህ ገደማ የደረሱ የሁሉም የባንክ ቅርንጫፎች በመላዉ ኢትዮጵያ እንዳሉ ገልጸዋል። 461 ቢሊዮን ብር ብድር መሰጠቱንም ተናግረዋል። ከዚህ ዉስጥም 85 በመቶኛዉ ለግል እንዲሁም ቀሪዉ 15 በመቶዉን ብድር መንግስት መዉሰዱን ጠቁመዋል።

በዲጂታል መንገድም እስካሁን ከ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ብድር መዉሰዳቸዉን ተናግረው ይህም ባንኮች ለህብረተሰቡ ከሚያቀርቡት ብድር በተሻለ ማሰራጨቱን ገልጸዋል።

የአጠቃላይ የሁሉም ባንኮች ሀብትም አሁን ላይ 2.9 ትሪሊዮን ብር መድረሱንም ጨምረዉ ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *