መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 29፤2015-የህዳሴ ግድብ ሙሌት እስከ መስከረም መጀመሪያ እንደማይከናወን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ

ኢትዮጵያ የሱዳንን እና ግብፅ ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የህዳሴ ግድብ ሙሌቱ እስከ መስከረም መጀመሪያ እንደማታከናዉን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ሀምሌ አጋማሽ የግድቡን የዉሃ ሙሌት ስናከብር ነበር ያሉት ጠ / ሚኒስትሩ ዘንድሮ ግን በቂ የዉሃ መጠን ለሁለቱ ሀገራት ከደረሰ በኋላ ሙሌቱ እንደሚከናወን መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር ሙሌት የተከናወነ ሲሆን በዘንድሮዉ ክረምት አራተኛዉ ሙሌት ለማከናወን እቅድ ተይዞ ነበር። ሆኖም ኢትዮጵያ የሁለቱ ሀገራትን ጥያቄ በማክበር ይህን እቅድ ማራዘሟን ነዉ ጠ/ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ሱዳን እና ግብፅ በተደጋጋሚ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ አሳሪ ስምምነት እንዲፈጸም ፍላጎት እንዳላቸዉ ሲገለጽ ቆይቷል። በተለይም ግብፅ ለአፍሪካ ኅብረት፣ ለአረብ ሊግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ለኃያላኑ ምዕራባውያን በተደጋጋሚ ከግድቡ ጋር በተያያዘ አቤቱታዋን ስታሰማ እንደነበር ይታወቃል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *