መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 3፤2015-ቱኒዚያ ጥቁር ስደተኞች ላይ በደል ትፈፅማለች በሚል የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

የቱኒዚያ መንግስት በመቶዎች የሚቆጠሩና ከሊቢያ  ድንበር ላይ የተያዙ ስደተኞችን ወደ ድንበር ስፍራ መመለሱን ተከትሎ በጥቁር አፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰውን ትችት እየቀረበበት ይገኛል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ግን ክሱን ውድቅ አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ካይስ ሰኢድ በትላንትናው እለት እንደተናገሩት ስደተኞቹ “እሴቶቻችን” ናቸው ሰብአዊ አያያዝ እያገኙ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ስደተኞች ግን የበረሃውን ሙቀት በትንሽ ምግብና ውሃ ለማሳለፍ እንደተገደዱ ይናገራሉ። ወደ አውሮጳ የፍልሰት ዋና መስመር የሆነችው ቱኒዚያ፣ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በመሰብሰብ ቱኒዚያን ከሊቢያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ወደሚገኝ የራቀ የመጠባበቂያ ቀጠና ያባረረች ሲሆን ከመብት ተሟጋቾች ዘንድ ትችት ደርሶባታል። የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት በሰጡት መግለጫ “እነዚህ ስደተኞች ከኛ እሴቶች እና ባህሪያት የሚመነጩ ሰብአዊ አያያዝ እየተቀበሉ ነው በማለት እየተነዛ ያለው ክስ የቅኝ ግዛት ኃይሎች እና ወኪሎቻቸው የሚያሰራጩት ነው” ብለዋል።

በፕሬዝዳንቱ መግለጫ ላይ የቱኒዚያ የጸጥታ ሃይሎች በሀገሪቱ ውስጥ መኖር የሚፈልጉ የውጭ ዜጎችን ከለላ እንደሚያደርጉ በመጥቀስ “ቱኒዚያ ለሽያጭም ሆነ ለኪራይ የቀረበች አፓርታማ አይደለችም” ሲል ያክላል። ሊቢያ በበኩሏ ቱኒዚያ ስደተኞቹን ከድንበር አካባቢ እንድታነሳ እንደምትፈልግ ተናግራለች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *