????ትብብር የተጠየቁት የአዲስ አበባ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋነተኞች በአንድ ቀን ውስጥ አስክሬኑን አግኝተዋል
በአማራ ብ/ክ/መ/ሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብር ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ሮቢ እየተባለ በሚጠራዉ ወራጅ ወንዝ ዉስጥ እድሜዉ 38 ዓመት የተገመተ ሰዉ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አስከሬኑን ያገኙት ትብብር የተጠየኩት የአዲስ አበባ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋነተኞች መሆናቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
በክልሉ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በቀረበ ጥያቄ መሰረት የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች ዛሬ ሀምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ሲሆን አስከሬኑን አግኝተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
የአካባቢው ፖሊስ መምሪያ አስከሬኑን ለሳምንታት ፈልገዉ ሲያጡ ለኮሚሽኑ ትብብር የጠየቁ ሲሆን ዋናተኞቹ ዛሬ ሄደዉ አስከሬኑን ለማግኘት ችለዋል።
በትግስት ላቀው